በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር የተመራ የህንድ የቴክኖሎጂ ተቋማት ልዑክ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መከረ፡፡
· Other
A delegation led by Anil Kumar engaged with the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to advance Ethiopia–India collaboration in artificial intelligence and digital infrastructure development.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በፈጣን እድገት ውስጥ መሆኑን ለልዑካኑ ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የልማት አጀንዳ ውስጥ በቴክኖሎጂው መስክ እያደገ የመጣውን የኢንስቲትዩቱን ሚና በማብራራት፥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል የለውጥ መሳሪያ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡
ኢንስቲቲዩቱ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ፣ ሁሉን አቀፍ እና ለሕዝብ ፍላጎቶች ምላሽ የሚሰጡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ዳታ ሴንተሮችን እና የተለያዩ ሲስተሞችን በማልማት ጠንካራ የዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ ያደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያ እና ህንድ ትስስርን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ ያደረገ መሆኑን ዶ/ር ወርቁ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማርበበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ዋነኛ የትብብር መስክ ለማድረግ ውይይቶች መደረጋቸውን አስታዉሰዋል፡፡ ዉይይቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
ልዑካኑ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ይዞት የመጣወን መልካም እድል እና በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን አስመልክቶ በህንድ ያለን ተሞክሮ አጋርተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ በህንድ ባሳለፍነው ወር በተደረገው የኤ.አይ ኢምፓክት ሰሚት ላይ ኢትዮጵያን ወክለዉ የተሳተፉ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ዘርፍ ያለውን ተሞክሮ አካፍለዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute