የኤ.አይ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ለምርታማነት ከፍታ
· AI Solutions
Micron Expands AI Chip Production to Drive Industrial Innovation, High-Performance Computing, and Global Economic Growth
የቴክኖሎጂ ዕድገት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ከኢንዱስትሪ ክፍለ ኢኮኖሚ ጋር ማስተሳሰሩ በተግባር የታገዘ ከፍተኛ ምርታማነትን እውን እያደረገ ይገኛል። ይህም በቴክኖሎጂውና በኢንዱስትሪው መካከል የተፈጠረው ጥብቅ ትስስር ለዓለም አቀፉ የፈጠራና የዕድገት ጉዞ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ያሳያል።
ሮይተርስ የዜና ወኪል ባወጣው መረጃ ታዋቂው የአሜሪካ የሜሞሪ ቺፕ አምራች ኩባንያ ማይክሮን ቴክኖሎጂ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥርዓቶች የሚያገለግሉ የከፍተኛ ፍጥነት ሜሞሪ (HBM) ቺፖችን በስፋት በማምረት ላይ ይገኛል። ኩባንያው ዘንድሮ ከፍተኛ የሆነ የገበያ ድርሻ እና የአክሲዮን ትርፍ እያስመዘገበ
መሆኑን ጠቅሷል፡፡
ይህ የተመዘገበው አስደናቂ ትርፍ የዎል ስትሪት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ቀደም ሲል ካስቀመጡት ግምትና ትንበያ እጅግ በልጦ የተገኘ ነው። ይህም በአሁኑ ወቅትየኤአይ ዳታ ማዕከላት ፍላጎት በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩና የሜሞሪ ቺፖች በከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊነታቸው ማደጉን ማረጋገጫ ሆኗል።
ከዚህ ስኬት በመነሳት ማይክሮን ቴክኖሎጂ የኤአይ መሠረተ ልማቶችን ይበልጥ ለማስፋፋትና ኢንቨስትመንቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።ይህ ሁኔታ ኤአይ በዘመናዊው የኢንዱስትሪ ዓለም ውስጥ ያለው ሚና የማይተካ፣ ወሳኝ እና የወደፊቱን የኢኮኖሚ መልክ የሚቀይር መሆኑን በግልጽ ያሳያል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute