በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የኢትዮጵያ እና ቤኒን የሁለትዮሽ ትብብር .
· Visiting
A high-level Beninese delegation led by Minister Mahouna Akplogan visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore cooperation in artificial intelligence, technology transfer and capacity building.
በቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርጓል።
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል አድርገዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን ለማሳካት እያከናወነ የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ስራዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እያከናወነ የሚገኘውን አህጉራዊ አርአያነት ያለው ተግባር አድንቀዋል። ሁለቱ ሀገራት በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ተመሳሳይ ራዕይና ጉዞ ያላቸው በመሆኑ በጋራና በትብብር መስራታቸው የሚፈለገውን ዘላቂ ልማት ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅት ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የኤአይ ቴክኖሎጂን በስፋት ስራ ላይ በማዋል የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ልምድ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም በቴክኖሎጂ ሽግግርና በአቅም ግንባታ ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ የጋራ አቅጣጫዎች ላይ መክረዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute