የሁለተኛ ዙር የኤ.አይ ስታርታፕ ኢንኩቤሽን ሰልጣኞች አቀባበል ተደረገላቸዉ።
· Education
EAII Startup Center Welcomes Second Cohort of Technology Startups for Incubation and Global Growth
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከል በተለያዩ የቴክኖሎጂ መስኮች ላይ ያተኮሩ አዳዲስ ስታርታፖችን ለሁለተኛ ዙር የኢንኩቤሽን ፕሮግራም ተቀብሏል። አዲሶቹ ሰልጣኞች በማዕከሉ በሚኖራቸው የቆይታ ጊዜ የስራ ቦታ፣ የመሰረተ ልማት፣ የስልጠና፣ የማማከር እንዲሁም የገበያ ትስስር እድሎችን የሚያገኙ ይሆናል።
በአቀባበል መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ስታርታፖቹን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሁለንተናዊ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የሚያገኟቸውን እድሎች በአግባቡ በመጠቀም የፈጠራ ሀሳቦቻቸውን ከሀገር ውስጥ አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በጂ.አይ.ዜድ ኢትዮጵያ የኤ.አይ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ተባባሪ መሪ ኤሊ ሳዋያ በበኩላቸው የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ተግባር ለመቀየር እንዲህ ያሉ ፕሮግራሞች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ጂ.አይ.ዜድ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የመጀመሪያው ዙር ሰልጣኞች የነበራቸውን ልምድና ተሞክሮ ያካፈሉ ሲሆን፤ ከዝግጅቱ ጎን ለጎንም አዲሶቹ ሰልጣኞች የኢንስቲትዩቱን የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የምርት ማሳያ ክፍል እና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute