የኦሮሚያ የሕግ ማሰልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
· Visiting
Institute and OLTRI discuss collaboration to advance AI-driven national development.
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዩ ዘውዴ ለስራ ኃላፊዎቹ የተቋሙን የስራ እቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
የኦሮሚያ የሕግ ማሰልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አዱኛ አሕመድ ጉብኝቱን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሀገርን በመገንባት ዙሪያ እየተሰራ ያለው ስራ የሚያኮራ እና የሚያስመሰግን ነው ብለዋል፡፡ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን እቅድ በአግባቡ ለመከወን ትልልቅ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ያስተዋሉበት ጉብኝት መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡
ጉብኝቱም በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በቴክኖሎጂው መስክ አብሮ መስራት የሚያችላቸውን መሰረት የጣለ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute