የፐብሊክ ሰርቪስ ችግሮችን የሚቀርፉ የኤ.አይ መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ ዉድድር ተካሄደ፡፡
· AI Solutions
EAII, AAU, and UNDP Host AI Innovation Competition to Advance Public Service Solutions
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዩ.ኤን.ዲ.ፒ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ውድድር የተለያዩ የፐብሊክ ሰርቪስን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ የኤ.አይ ፈጠራ ውጤቶች ቀርበውበታል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በውውድር መድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ዉድድርና ሽልማት ገና ጅማሮ ሲሆን፤ በቀጣይም እንዲህ ያሉ የሕዝብን ችግሮች የሚፈቱ የኤ.አይ የፈጠራ ዉጤቶች የሚቀርቡበት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በመልዕክታቸው በውድድሩ አሸንፈው የተሸለሙ የመፍትሔ ሀሳቦች ወደ ተግባር ሊለወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ለሁለት ቀናት በተካሄደው ውድድር 16 የኤ.አይ ፈጠራዎች ለውድድር ቀርበው ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለወጡት የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በውድድሩ አንደኛ ለውጣው ቡድን ግማሽ ሚሊዮን ብር፣ ለሁለተኛው 3 መቶ ሺህ እንዲሁም ለሦስተኛው ቡድን ደግሞ 2 መቶ ሺህ ብር ተበርክቷል፡፡
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ስታርታፕ ማዕከል እየሰለጠኑ የሚገኙ ስታርታፖች በውድድሩ ካሸነፉት መካከል ይገኙበታል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute