የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኞች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኝተዋል፡፡
· Visiting
Addis Ababa Transport Bureau Explores AI Solutions with EAII to Modernize Urban Mobility and Improve Traffic Efficiency
ሰራተኞቹ በኢንስቲትዩቱ ያዩት እውነታ ከጠበቁት በላይ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል። ተቋሙ እየገነባቸው ያሉ የቴክኖሎጂ አቅሞች ሀገሪቱ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸውን በአካል ለመታዘብ መቻላቸውን አብራርተዋል። ቀደም ሲል ስለ ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ አማራጮች የማየትና የመስማት ዕድል ነበረን ነገር ግን በአካል ሲሆን ይለያል ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ከትራንስፖርት ሲስተም ጋር በማስተሳሰር የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ማቃለል እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡ ቴክኖሎጂው በተለይም የትራፊክ መጨናነቅን በዘመናዊ መንገድ ለመቀነስ፣የአደጋ ስጋቶችን አስቀድሞ ለመለየት እና ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተቀላጠፈና የተሳለጠ የትራንስፖርት ሥርዓት ለመዘርጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመላክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute