አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ድሮኖች አረምን ለመከላከል እየረዱ ነው፡፡
· AI Solutions
Researchers at the Royal Agricultural University have developed an AI-powered drone system that detects weeds in crop fields and enables precise herbicide application, reducing chemical use, costs, and environmental impact.
በእንግሊዝ የሚገኘው የሮያል ግብርና ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች አርሶ አደሮች አረምን በዘመናዊ መንገድ የሚከላከሉበትንቴክኖሎጂ ይፋ አደረጉ።
ይህ ቴክኖሎጂ ድሮኖችን እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስንበመጠቀም በእርሻ ማሳ ውስጥ የሚገኙ አረሞችን በትክክል ለይቶ ለማወቅ ያስችላል። ይህም የኬሚካል አጠቃቀምን በመቀነስ መድኃኒት በሙሉ ማሳ ላይ ከመርጨት ይልቅ አረም ባለበት ቦታ ላይ ብቻ እንዲያርፍ ያደርጋል።
ይህ ቴክኖሎጂ ለአርሶ አደሮች አስቸጋሪ እና ረጅም ጊዜ የሚወስደውን አረምን የመከላከል ስራ በአጭር ጊዜ ያከናውናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች እንዳስታወቁትበዚህ ቴክኖሎጂ አረሞች የሚገኙበትን ቦታ በትክክል መለየት ይቻላል። ይህም ለጠቅላላው እርሻ ፀረ-ተባይ ወይም ፀረ-አረም ከመጠቀም ይልቅ ለሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ብቻ ለመጠቀም ያስችላል፡፡
ቴክኖሎጂው ወደ አፈርና ውሃ የሚቀላቀሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን በመቀነስ የተፈጥሮ ሚዛንን ከመጠበቁ በተጨማሪ አነስተኛ ኬሚካል ጥቅም ላይ በማዋል የአርሶ አደሩን የምርት ወጪ ይቀንሳል።
እንደ ቢ.ቢ.ሲ ዘገባ በዩኒቨርሲቲውየሚገኙ ተማሪዎች በአሁኑ ወቅት ከተዘሩ ሰብሎች መካከል የተለያዩ የአረም አይነቶችን በትክክል ለይተው የሚያውቁ የኤ.አይ ፕሮግራሞችን እያሰለጠኑ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute