"በሌሎች ሀገራት ያየናቸውን አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ልጆች ተሰርተው በኢንስቲትዩቱ በማየታችን ደስ ብሎናል" ፓስተር ጌትነት ለማ
· Visiting
Ethiopian Council of Gospel Believers Churches Explores AI Collaboration to Advance Digital Transformation and Institutional Efficiency
ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ዋና መስሪያ ቤት የተውጣጡ አመራር እና ሰራተኞች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
ኢንስቲትዩትን ጎበኝተዋል።
የካውንስሉ ዋና ጸሐፊ ፓስተር ጌትነት ለማ ቀደም ሲል በሌሎች ሀገራት ያዩዋቸውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ልጆች ተሰርተው በኢንስቲትዩቱ ውስጥ በማየታቸው ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸዋል።
ፓስተሩ አክለውም ኢንስቲትዩቱ ለተለያዩ ተቋማትና ዘርፎች እያበረከተ ያለውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ስራዎች መመልከታቸውን ገልጸው፤ በካውንስሉ ስር አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማት ፈጣንና የተሳለጠ አሰራር እንዲኖራቸው ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ በመስራት ምቹ አሰራር ለመዘርጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
በጉብኝት መርሃ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዋና የዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊና የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች በተመለከተ ለጎብኝዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute