የአልጄሪያ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑካን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ፡፡
· Visiting
Algerian military delegation explored the Institute’s AI technologies and innovation facilities.
በጄኔራል ተፋሂ ላይድ የተመራ የአልጄሪያ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ልዑክ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ለጎብኚዎቹ ስለዋና መስሪያ ቤቱ እና የኢንስቲትዩቱ ስራዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ለስታርታፖች የሰጠውን ልዩ ትኩረት እንዲሁም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ የሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ ለልዑካኑ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት የኢንስቲትዩቱን የምርት ማሳያ ክፍል፣ የስታርታፕ ማዕከል፣ የሮቦቲክስ ወርክ ሾፕ እንዲሁም የሆሎግራም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑካኑ በጉብኝታቸው ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው፥ ኢንስቲትዩቱ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ በዚህ ልክ መስራቱን አድንቀዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute