"የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከሉ ወጣቶች ራዕያቸውን ወደ ተግባር የሚቀይሩበት ምቹ ስፍራ ነው" — አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ
· Visiting
French Ambassador Visits EAII to Advance Tech Cooperation, Youth Innovation, and Economic Productivity.
በኢትዮጵያየፈረንሳይ አምባሳደርአሌክሲስ ላሜክ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አድርገዋል።አምባሳደሩ በጉብኝታቸውወቅት ኢንስቲትዩቱ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ችግሮች ለመፍታት እያከናወነ ያለውን የቴክኖሎጂ ልማት ስራ አድንቀዋል።
በኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋናዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) አማካኝነትማብራሪያ የተሰጣቸውአምባሳደሩ፣ በተለይም በስታርታፕ ማዕከሉ ወጣቶችን ለመደገፍ
የሚደረገው ጥረት ትልቅተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።
"ማዕከሉ ወጣቶች የፈጠራ ሀሳባቸውን መሬት እንዲያወርዱ የሚያስችል እውነተኛ ቦታሆኖ አግኝቼዋለሁ" ሲሉ አምባሳደር ላሜክ አስተያየታቸውንሰጥተዋል።
በመጨረሻም በፈረንሳይእና በኢትዮጵያ መካከል በቴክኖሎጂው ዘርፍ በመንግስትምሆነ በግሉ ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከርቀጣይነት ያላቸው ውይይቶች
እንደሚደረጉ አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute