የUNESCO የኤ.አይ ዝግጁነት ምዘና ሪፖርት ከፍተኛ የፖሊሲ ምክክር ተካሄደ፡፡
· Other
EAII, UNESCO, and EU Launch AI Governance Report to Advance Ethical Innovation and Digital Transformation in Ethiopia
ኢትዮጵያ በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፍዓለማቀፍ ትኩረትን እየሳበች መሆኗን የሚያረጋግጥሁነት ዛሬ ተካሂዷል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻልኢንተለጀንስ
ኢንስቲትዩት፣ዩኔስኮ እና የአውሮፓ ህብረት በጋራ ባዘጋጁት ከፍተኛ የፖሊሲ ምክክር መድረክ ላይ UNESCO AI Readiness Assessment (RAM) Report ይፋ ሆኗል። ይህ ሪፖርት ለኢትዮጵያ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት ስትራቴጂካዊፍኖተ ካርታ ሆኖ እንደሚያገለግል ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በኤ.አይ ዙሪያ ወደፊት
ለምትወስዳቸው እርምጃዎች ጽኑ መሠረት እንደሚጥል ገልጸዋል። ለጥናቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ጥልቅምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የዩኔስኮ በኢትዮጵያ የላይዘን ቢሮ ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ሪታ ቢሱናት (ዶ/ር) ይህ ሪፖርት ኢትዮጵያ ከዓለማቀፍ ተቋማት ጋር ምን ያህልጠንካራ ተቋማዊ ትብብር መዘርጋት እንደምትችልያሳየ ጉልህ ማስረጃ መሆኑን አስምረዋል። "ኤ.አይያለ ሥነ-ምግባር መርሆች ውጤታማ አይሆንም"
ያሉት ዶ/ርሪታ፥ ሪፖርቱን እንደ ፖሊሲግብዓት ተወስዶ ምክረ ሃሳቦቹ ወደ ተግባር ሊሸጋገሩ ይገባል ብለዋል።
ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የኤ.አይቴክኖሎጂ ትግበራን የሚያዘገዩ ማነቆዎችን ከሥር መሠረቱ ለይቶ አቅርቧል።ይህንን ክፍተት ለመቅረፍ የተደራሽነት፣ የድጋፍ አሠጣጥ፣ የአቅም ግንባታ እና የመሠረተ ልማት ማጠናከሪያምክረ ሃሳቦች ቀርበዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችሰፋ ያለ ክርክርና የሃሳብልውውጥም የምክክሩንዋጋ ይበልጥ ያሳደገ ሆኗል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute