የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
German Foreign Office Director-General Visits EAII to Explore Bilateral Cooperation in Artificial Intelligence
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማዕከላዊ አገልግሎቶች ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፒር ገባውር በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።
በአፍሪካ ጉዳዮች፣ በልማት ትብብር እና በዲፕሎማሲ የረጅም ዓመት ልምድ ያላቸው ዶ/ር ፒር ገባውር ያደረጉት ይህ ጉብኝት፤ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር፣ በፈጠራ ሥራዎች እና በዓለም አቀፍ አጋርነት ዙሪያ ያተኮረ ነው።
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ምርምርና ልማት፥በሰዉ ኃይል ልማት እንዲሁም በኤአይ መሰረተልማት ዙሪያ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን አስረድተዋል።
በተጨማሪም ዘርፉን ለመምራትና ለማልማት በስነምግባርና አስተዳደራዊ ጉዳዮች እና በተለያዩ ዘርፎች ኢትዮጵያ እያከናወናቸው ስላሉ ሥራዎች እና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute