በኤአይ በታገዘ አዲስ የቴክኖሎጂ ግኝት የጣፊያ ካንሰር ሳይባባስ ቀድሞ ማወቅ ተቻለ
· AI Solutions
AI Detects Early Signs of Pancreatic Cancer on CT Scans More Than a Year Before Diagnosis
በታዋቂው የሕክምና ጆርናል Gut ላይ የወጣው ይህ አዲስ ጥናት እንደሚያመለክተው፤ ይህ መላ በሲቲ ስካን ምስል ላይ በባለሙያዎች ዓይን የማይታዩ ጥቃቅን የሕብረ ሕዋስ ለውጦችን በመለየት ካንሰሩ በይፋ ከመረጋገጡ በአማካይ ከ 475 ቀናት ወይም ከአንድ ዓመት ከ 3 ወር በፊት መለየት ችሏል።
የኤአይ ቴክኖሎጂው የበሽታ ምልክቶችን የመለየት አቅም 73 በመቶ ነው፡፡ ከራዲዮሎጂ ስፔሻሊስቶች ሲነጻጸር እነርሱ ማወቅ የቻሉት 39 በመቶ ብቻ ነው።
ተመራማሪዎቹ እንደሚናገሩት የጣፊያ ካንሰር በአብዛኛው በጊዜ ስለማይታወቅ የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ከሆኑ የካንሰር ዓይነቶች አንዱ ነው።
ይህ ቴክኖሎጂ ግን በሽታው ገና በቅድመ ደረጃ (Stage 0) ሳለ እንዲታወቅ በማድረግ የመዳን እድልን ከሁለት እጥፍ በላይ ከፍ የሚያደርግ ነው፡፡የባለሙያዎችን የሥራ ጫና በመቀነስ የህክምና ጥራትንም ያሳድጋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute