የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ዘመን ባንክ በፋይናንስ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አካሄዱ::
· Other
EAII and Zemen Bank Explore AI Partnership to Accelerate Financial Innovation, Digital Transformation, and Productivity
የዘመን ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ በጉብኝቱም ሁለቱ ተቋማት በፋይናንሻል ዘርፉ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅት ኢንስቲትዩቱ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ያበለጸጋቸውን የተለያዩ ሥርዓቶች እና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ለባንኩ አመራሮች ዝርዝር ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በተጨማሪም የባንኩ የስራ ኃላፊዎች በኢንስቲትዩቱ የሚገኙትን የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የምርት ማሳያ ክፍል እና የኤ.አይ ስታርትአፕ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
የዘመን ባንክ የሪቴል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ አስራት ታደሰ በኢንስቲትዩቱ ተስፋ ሰጪ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸው፣ በቀጣይም ባንኩ የአሰራር ሂደቱን በቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማዘመን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡አቶ አስራት አክለውም፣ በኢንስቲትዩቱ የታቀፉ ስታርትአፖች ችግር ፈቺ እና በተለያዩ ዘርፎች በተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ለመታዘብ መቻላቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ዘርፎች ሀገር በቀል የሆኑ የሰው ሰራሽ አተውሎት መፍትሄዎችን ለማምጣት እያከናወነ ያለውን ስራ አብራርተዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የፋይናንስ ዘርፉን በዘመናዊ አሰራር ለመደገፍ ከባንኩ ጋር በቅርበት ለመስራት በኢንስቲትዩቱ በኩል ከፍተኛ ፍላጎትና ዝግጁነት መኖሩንም በውይይቱ ወቅት አረጋግጠዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute