ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል (GITEX GLOBAL) 2025 መካሄድ ጀመረ፡፡
· Other
GITEX GLOBAL 2025 Unites 180 Nations in Dubai to Explore AI, Deep-Tech, and the Future of Global Innovation.
የዓለም ትልቁ የቴክኖሎጂ ሁነት ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል (GITEX GLOBAL) መካሄድ ጀምሯል፡፡ ከኦክቶበር 3 እስከ 17፣ 2025 ለ45ኛ ጊዜ እየተካሄድ የሚገኘው ጂ.አይ.ቴክስ 2025 (Gitex 2025) በዱባይ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በሁነቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ180 ሀገራት የተውጣጡ ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡ 6500 የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች፣ 1800 ስታርታፖች እና 1200 ባለሀብቶችም ተሳታፊ ናቸው፡፡
በዘንድሮው ሁነት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች፣ ዲጂታል የጤና አጠባበቅ፣ የሳይበር ደህንነት እና ስማርት ሲቲን የሚዳሰሱ ጉዳዮች በመድረኩ ዐብይ ጉዳይ ሆነው ይነሳሉ፡፡
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሁነቱ ማዕከላዊ ርዕሰ ጉዳይ መሆኑን የሁነቱ ድረገጽ አስነብቧል፡፡ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ውጤቶችም የዝግጅቱ አንድ አካል በሆነው ኤግዚብሽን ላይ እየቀረቡ ነው፡፡ ይህ ዓለማቀፍ ሁነት የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ተፅዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ስለመምጣቱ ማሳያ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute