የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች 22ኛውን ዓለማቀፍ የፀረ ሙስና ቀን አከበሩ፡፡
· Other
EAII Marks International Anti-Corruption Day with Focus on Ethics and Institutional Integrity
“ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር‘’ በሚል መሪ ቃል በተቋሙ የተከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው ሙስና ረቂቅና ውስብስብ መሆኑን ጠቅሰው፥ትውልድን በሥነ-ምግባር በማነፅ የእድገት ፀር የሆነውን ሙስና መዋጋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አክለውም ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ ተቋማት አሰራርን ዲጂታል በሆነ መንገድ እንዲያዘምኑና ቴክኖሎጂን እንዲታጠቁ በማለት፣ ለአብነት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን አንስተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የሙስና መንስኤዎችና መፍትሄዎቹን የተመለከተ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በተጨማሪም የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች የሃብት ምዝገባ ሰርተፊኬታቸውን በፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የኮሚሽነሩ የሕግ አማካሪ ለሆኑት የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ተስፋዬ በየነ አስረክበዋል፡፡
በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ አመራር እና ሰራተኞች ብልሹ አሰራርን ለመዋጋት የሚያስችል ባለ5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የዕለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute