አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰውን ልጅ ሥራ ከመንጠቅ ይልቅ እንደሚያሻሽል አዲስ ጥናት አመለከተ፡፡
· AI Study
Study finds AI is more likely to enhance human jobs than replace them, highlighting the future of human-machine collaboration.
የአርቲፊሻልኢንተለጀንስ (ኤ.አይ) መስፋፋት የሰውን ልጅ ከሥራ ገበታያሰናብታል የሚለው ስጋት በዓለም ዙሪያ ቢናኝምየጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው አዲስ ጥናት ግንተቃራኒውን ውጤት አመልክቷል። ቴክኖሎጂው የሰውን ልጅ ሚናከመተካት ይልቅ የሥራ አፈጻጸምንየሚያሻሽልና አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር መሆኑን ጥናቱ ይፋ አድርጓል።
እንደጥናቱ ትንተና ኤ.አይ ተደጋጋሚ እና በመረጃ ትንተና ላይ የተመሰረቱተግባራትን በከፍተኛ ፍጥነት በማከናወን የሰውን ልጅ የሥራ ጫና ይቀንሳል። ሆኖም እንደ ሂስዊ አስተሳሰብ፣ ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና ጥልቅ ስሜታዊ ግንኙነትን የመሰሉ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ክህሎቶች በማሽኖች ሊተኩ እንደማይችሉ ተረጋግጧል።
ባለሙያዎችእንደሚሉት የወደፊቱ የሥራ ዓለም ሰውበኤ.አይ የሚተካበት ሳይሆን፤ ሁለቱ ተቀናጅተው ምርታማነትን የሚጨምሩበት ይሆናል።
ቴክኖሎጂውአንዳንድ ነባር የሥራ መደቦችንቢቀንስም በምትኩ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ክህሎት የሚጠይቁ አዳዲስ ዘርፎችን እንደሚፈጥር ይጠበቃል። በመሆኑም ሠራተኞች ራሳቸውን ከቴክኖሎጂው ጋር በማላመድ እና አዳዲስዲጂታል ክህሎቶችን በማዳበር ለተለዋዋጭው የሥራ ገበያ መዘጋጀትእንዳለባቸው ጥናቱ ያሳስባል።
የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም የ2020 (እ.ኤ.አ) መረጃ እንዳመላከተው በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በዓለም ዙሪያ 85 ሚሊዮን የሥራ አጥነት ሊያጋጥም ቢችልም፤ ኤ.አይን የመሳሰሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ግን እስከ 97 ሚሊዮን የሚደርስ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራሉ፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute