“የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ ዕድል ነው።” አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ
· Other
Ethiopia Marks the Day of Tomorrow with a Call for Responsible AI, Digital Sovereignty, and Inclusive Technological Transformation
“ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ነገን ዛሬ መገንባት” በሚል መሪ ቃል ጳጉሜን5 የነገ ቀን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበትበሳይንስ ሙዚየም ተከበረ።
የበዓሉ የክብር እንግዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዓሉን አስመልከቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያዕድል ነው ይህንን ተገንዝቦ በኃላፊነት መምራት ያስፈልጋል ብለዋል። የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የመንግስታትን፣ የተቋማትን እና የዘርፎችን እድገት እየለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ተቀባይ ብቻ ሆና መቀጠል አትችልም። የነገ ቀንን ስናከብር ሀገሪቱ የዲጂታል ሽግግሩ ላይ የሰራችውን ስራ የምንመረምርበት እና ለነገዋ ኢትዮጵያ ልምዶችን የምንወስድበት ነው ብለዋል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ዕለቱን አሰመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገሪቱ በተገበረችው የዲጂታል ሽግግር የተቋማት ቅንጅት፣ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት እና ፍትሃዊነት እንዲሁም የዜጎች በቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው መተማመን ለተገኙ ስኬቶች ወሳኝነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የዲጂታል ሽግግር ወቅት የነበሩ ተሞክሮዎችን እና የመረጃ ሉዓላዊነትን አስመልክቶ የፓናል ዉይይት ተካሂዳል። በፓናሉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይ ስኬታማ እንዲሆን በምርምርና ልማት ያገኛቸውን ድሎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute