ጋና የኤ.አይ የማስተማርያ ሥርዓቶችን በትምህርት ቤቶች ዉስጥ ተግባራዊ ልታደርግ ነዉ።
· AI Solutions
Ghana partners with Google to deliver AI-powered education in local languages nationwide.
የጋና መንግሥት የኤ.አይ ሥርዓቶችን በትምህርት ሥርዓቱ ዉስጥ ለማካተት የሚያስችል ትብብር ከጉግል ኩባንያ ጋር አድርጓል።
በስምምነቱ መሰረት በጋና የሚገኙ የትምህርት ይዘቶችን ወደ ሀገር ዉስጥ ቋንቋዎች በመቀየር በቀላሉ ለማስተማር የሚያግዙ የኤ.አይ ሥርዓቶች ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል።
ስምምነቱ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ የታገዘ ፍትሐዊ እና አካታች የሆነ ትምህርት ያለምንም የቋንቋ ልዩነት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነዉ።
እነዚህ ሥርዓቶች ያለምንም ክፍያ የሚቀርቡ መሆናቸዉን የአይ.አፍሪካ ድረ ገጽ መረጃ ያመላክታል። በተጨማሪም ከጋና የትምህርት ሥርዓት ጋር በማቀናጀት ስለ ስነ ምግባራዊ ኤ.አይ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችሉ ይዘቶች የሚካተቱበት ይሆናል።
በዚህም ሀገሪቷ የትምህርት ተደራሽነትን ለማሻሻል ከምታደርጋቸዉ እንቅስቃሴዎች መካከል ይሆናል ተብሏል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute