የኤ.አይ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የ3 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ እንዲቋቋም ጥሪ ቀረበ፡፡
· AI Investment
UN Secretary-General calls for $3 billion global AI fund to support developing nations.
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መጻዒ ዕድል ለሀብታም ሀገሮች እና ለተወሰኑ ባለሀብቶች የሚተው ጉዳይ አለመሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ፡፡ ዋና ጸሐፊው በሕንድ በተካሄደው የኤ.አይ ኢምፓክት ኮንፈረንስ ላይ ዓለማቀፍ ፈንድ በማሰባሰብ ታዳጊ ሀገራትን ከቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ማድረግ እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዚህም የአቅም ግንባታ፣ የኮምፒውቲንግ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ብሎም አካታች የሆነ የቴክኖሎጂ ሥነ ምህዳር መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውበታል፡፡ ተገቢው መዋዕለ ንዋይ በዘርፉ ካልፈሰሰ በርካታ ሀገራት ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ሊወጡ እንደሚችሉም አንስተዋል፡፡
ለማሰባሰብ የታለመዉ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም የአንድ ቴክኖሎጂ ኩባንያ አመታዊ ገቢ አንድ ፐርሰንት በታች መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልማት በአግባቡ እንዲመራ ለማድረግ እያደረገ ያለውን ጥረት በተመለከት በተለይም ባለፈው ዓመት በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነጻ ዓለም አቀፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሳይንሳዊ ፓናል መቋቋሙን ዋና ጸሐፊው አስታዉሰዋል፡፡
40 ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂውን ባለሙያዎች ያቀፈው ፓናሉ የኤ.አይ ስጋቶችን፣ እድሎችን እና የማህበራዊ ተፅዕኖዎችን በመተንተን ማስረጃዎችን ለማጋራት እና የእውቀት ክፍተቶችን ለመሙላት እንደሚሰራ የተ.መ.ድ ድረገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute