በሌሎች ሀገራት የሚታወቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በኢንስቲትዩቱ ተሰርተው መመልከታቸው እንዳኮራቸው የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የስራ ኃላፊዎች ገለፁ፡፡
· Visiting
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ለኃላፊዎቹ ገለፃ አድርገውላቸዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በማብራሪያቸው በተለያዩ መስኮች ችግሮችን መፍታት የሚችሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማልማት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የደረጃዎች…

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሰረት በቀለ (ዶ/ር) ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ኢንስቲትዩቱ ሀገራችን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን እየሰራ ያለውን ሰፊ ስራ በጉብኝታቸው መመልከታቸውን ተናግረዋል። በሌሎች ሀገራት የሚታወቁና ወደ ሀገራችን ቢመጡ ብለው የሚመኟቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች በኢንስቲትዩቱ ለምተው መመልከታቸው እንዳስደነቃቸው ዳይሬክተሯ በንግግራቸው ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ስራዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተቃኙ እንዲሆኑ እና በቀጣይነት በጋር ለመስራት ጉብኝቱ መንገድ የቀየሰ ስለመሆኑም ተመላክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute