ቻይና እ.ኤ.አ እስከ 2030 በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዓለምን ለመምራት እየገሰገሰች ነው
· Other
China Accelerates AI and Technology Self-Reliance as Ethiopia Pursues African Leadership by 2030
የብሉምበርግ ዘገባ እንዳመላከተው ቻይና እስከ በኤአይ ሞዴሎች እና በሌሎች ቁልፍ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ዓለምን በግንባር ቀደምትነት ለመምራት የሚያስችላትን ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች ነው።
ምንም እንኳን የምዕራባውያን ማዕቀቦች እና የሴሚኮንዳክተር ማይክሮቺፕ እገዳዎች ቢኖሩባትም ሀገሪቱ የቴክኖሎጂ አቅሟ በማጠናከር ረገድ አስደናቂ እመርታ
እያስመዘገበች ነው። የቻይና የቴክኖሎጂ ተቋማት እና ኩባንያዎች በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የውጭ ጥገኝነትን ለመቀነስ እየሰሩ ነው።
በላቀ የቴክኖሎጂ ምርምር፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና በመረጃ አሰባሰብ ረገድ ያላት ግዙፍ አቅም ቻይናን በዘርፉ ቀዳሚ ያደርጋታል። በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ ታዳሽ ኃይል እና በሮቦቲክስ ዘርፍ የምታሳየው የበላይነት ለዚህ የኤአይ እድገቷ ትልቅ አጋዥ ሆኗል።
ይህ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የቴክኖሎጂ ውድድር የበለጠ እንደሚያፋጥነውና የቀጣዩን አስር ዓመት የዲጂታል ኢኮኖሚ መልክ እንደሚቀይረው ተገምቷል። ኢንስቲትዩታችንም ኢትዮጵያን እ.ኤ.አ እስከ 2030 በሰው ሰራሽ አስተውሎት በአፍሪካ ግንባር ቀደም ለማድረግ እየሰራ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute