ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ራዕይ በሶስተኛው ሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ አቀረቡ
· Other
Prime Minister Abiy Ahmed Calls for Russian Academic Partnerships to Advance Ethiopia’s AI Vision and African Data Sovereignty
የኢትዮጵያጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በሶስተኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ ያላትን ራዕይ
በማስረዳት ከሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ጋር በትምህርትናበምርምር መስኮች የጋራትብብር እንዲደረግጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ የቴክኖሎጂ ትብብር መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ባለፈ፣ እነዚህን ሥርዓቶች ማስተዳደር፣ማስኬድና መቆጣጠር የሚችሉ
የሀገርውስጥ ባለሙያዎችን ማፍራት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በዘመናችን የእውቀትና የቴክኖሎጂአቅም ማለት በከፍተኛ ደረጃከሰው ሠራሽ አስተውሎት ጋር
የተያያዘ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኤአይ ቴክኖሎጂዎች አሁንባለው መንገድ መገንባታቸው የትኞቹ ቋንቋዎች በቴክኖሎጂው
እንደሚወከሉና የማን ማንነትና ተሞክሮ እንደሚካተትእንደሚወስን ገልጸዋል።
“አንድ አፍሪካዊ ተመራማሪ በሕዝባችን ቋንቋ የኤአይ መፍትሔዎችን መፍጠር መቻል አለበት። ተቋሞቻችንም እነዚህ መፍትሄዎች የእኛን መረጃ እንዴት
እንደሚጠቀሙ መወሰን አለባቸው” በማለት የአፍሪካ ቋንቋዎችናየመረጃ ባለቤትነትያላቸውን ወሳኝ ሚናአጉልተዋል።
በተጨማሪምኢትዮጵያ የመደመር የሰውሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ (Medemer University of Artificial Intelligence) እያቋቋመችመሆኑን
ያስታወቁትጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎችናተቋማት በማስተማርናበምርምር ከኢትዮጵያጋር እንዲሠሩ ጋብዘዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፈጠራና ምርምር በላቦራቶሪዎች ውስጥ ብቻ ተወስነው መቅረት እንደሌለባቸው፣ወደ ምርትና ንግድ ተግባራዊ
ሥራዎች መሸጋገር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute