ለፌደራል ተቋማት የመንግስት ሰራተኞች የኤ.አይ ክህሎት ስልጠና ተጀመረ።
· Education
AI for Government Programme Equips Federal Employees to Accelerate Digital Transformation, Productivity, and Public Service Innovation
ይህስልጠና በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በዩ.ኤን.ዲ.ፒ የጋራትብብር የተዘጋጀ ነው።
"AI for Government’’ በሚል ርዕስለተከታታይ ሰባት ቀናት በሚቆየውስልጠና የፌደራል ተቋማት የመንግስት ሰራተኞች የኤ.አይ ቴክኖሎጂንከዕለታዊ የስራ ክንዉናቸዉ ጋር በማቀናጀትየተሻለ ዉጤታማ የሚሆኑበትን አሰራር አመላካች ነዉ።
ሰልጣኞች መሰረታዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ክህሎቶችን፣ የዳታ ምንነትና ጠቀሜታ እንዲሁም በስራ መደባቸዉላይ አጋዥ የሆኑ የቴክኖሎጂዉዉጤቶችን በስፋት የሚዳሰሱበት ይሆናል።
ኢትዮጵያ የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታልሥርዓት ለመለወጥ በምታደርገዉ ጉዞ የመንግስት ተቋማት እና ሰራተኞችዋነኛ ተዋናዮች ናቸዉ።
የስራጫና እና ድግግሞሽ ባለባቸዉ ቦታዎች ለሚሰሩ ባለሙያዎች የኤ.አይቴክኖሎጂ ክህሎትን በማስጨበጥ የአሰራር ቅልጥፍናን መጨመር፣ ተወዳዳሪነትን ከፍ ማድረግ ብሎም የታለመዉንየዲጂታላይዜሽንጉዞ ከግብ ለማድረስ ያስችላል።
ስልጠናው ከዚህ ቀደምበሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርለሚገኙ የመንግሥት ሰራተኞች መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute