“የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሚያስደምም እድገት ላይ ነዉ።“ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌፍተናንት ጀነራል ጥጋቡ ይልማ
· Visiting
A delegation from the Defense Health Directorate led by Tegabu Yilma visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore collaboration in applying AI technologies to modernize military healthcare services.
የመከላከያ ጤና መምሪያ ከፍተኛ መኮንኖች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ። በጉብኝቱ ኢንስቲትዩቱ ያለማቸዉን የተለያዩ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ ዉጤቶች ተጎብኝተዋል። በተለይም የኤአይ እና ሮቦቲክስ ማምረቻ ክፍል (ወርክሾፕ)፥የምርት ማሳያ ክፍል (ሾዉሩም) እንዲሁም ስታርታፕ ማእከሉን አስመልክቶ ለጎብኝዎች ገለፃ እና ማብራሪያ ቀርቧል።
ጉብኝቱን የመሩት የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌፍተናንት ጄነራል ጥጋቡ ይልማ በበኩላቸዉ ኢንስቲትዩቱ ዉጤታማ ስራ እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። “የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሚያስደምም እድገት ላይ ነዉ።“ ያሉት ጄነራሉ “የኢንስቲትዩቱ ስኬታማ ስራዎች የሀገራችንን ተቋማት አሰራር በማዘመን የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣሉ” ብለዋል። በተለይም በጤናዉ ዘርፍ የተከናወኑ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ ዉጤቶች የጤናዉን ዘርፍ ለማዘመን የሚያግዙ በመሆናቸዉ በመከላከያ ሆስፒታሎች እንዲተገበሩ ለማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩም አስረድተዋል።
ኢንስቲትዩቱ ዋና መምሪያዉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ላከናወናቸዉ ተግባራት የምስጋና ሽልማት ተበርክቶለታል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute