የዛምቢያ መከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አደረገ፡፡
· Visiting
Zambian Defence Delegation Commends Ethiopia’s Progress in AI and National Innovation
በዛምቢያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄነራል ጆፈሪ ዚይሌ የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ለልዑካን ቡድኑ በኢንስቲትዩቱ የሚሰሩ የምርምር ውጤቶች እና የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ ልዑካኑ በጉብኝታቸው የሮቦቲክስ እና የስታርታፕ ማዕከላትን ጨምሮ የምርት ማሳያ ክፍሎችን ተዘዋውረዉ ተመልክተዋል።
የዛምቢያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄነራል ጆፈሪ ዚይሌ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት በኢንስተትዩቱ የተመለከቱት የስራ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን ህይወት ለማቅለል ጥቅም ላይ እየዋለ እንዲሚገኝ በጉብኝታቸው መገንዘባቸውን በመግለጽ ሀገሪቱ ለመሰረተ ልማት ግንባታ የሰጠችው ትኩረት እንዳስደነቃቸውም ተናግረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute