ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ስኬት ለማስቀጠል ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ
· AI Solutions
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute launched the Clean Ethiopia app to help citizens report pollution and support environmental protection through AI.
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ "የፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" ንቅናቄ ዘላቂ ልማትን በተግባር ማሳያ መሆኑን ገለጹ። የአካባቢ ብክለት ከዜጎች ጤና ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረው የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን የአፍሪካ አርአያ እያደረጋት እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮው 3ኛ ዓመት ንቅናቄ ቀጣይ ስኬት የሚወሰነው እርምጃ ነውም
ብለዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኤ.አይ ቀጣይነት ላለው ክትትል፣ የብክለት ባህሪን ለመለየት፣ አስቀድሞ ትንበያ ለመስጠትና በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ፈጣን የቅድመ-ውሳኔ ስራዎችን ለማሳለፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ኢንስቲትዩቱ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "Clean Ethiopia" መተግበሪያን (App) ከአፕ ስቶር ስቶር
በማውረድ ዜጎች ያሉበት ቦታ ሆነው ብክለትን ሪፖርት እንዲያደርጉ፣ በዘመቻዎች ላይ እንዲሳተፉና የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴዎችን እንዲከታተሉ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ማህበረሰቡ መተግበሪያውን አውርዶ በመጠቀም ለፅዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያ ግንባታ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute