“AI for Government” በሚል ርዕስ ለፌደራል የመንግሥት ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
· Education
AI for Government Programme Concludes, Empowering Public Servants to Drive Digital Transformation and Institutional Productivity
ላለፉት ስድስት ቀናት “AI for Government” በሚል መሪቃል ለፌደራል ተቋማት የመንግሥት ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። ስልጠናው ሰራተኞች የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በተቋም ስራዎቻቸው ውስጥ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ ግንዛቤ ያስጨበጠ ነው።
መርሃ ግብሩ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እናበተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የጋራ ትብብር የተዘጋጀ
ነው፡፡ ስልጠናው የተሰጠውም በሶስቱ ተቋማት አስተባባሪነት በሚንቀሳቀሰው ኤ.አይ ዩኒፖድ ስር ነው።
በማጠቃለያው ላይ ንግግር ያደረጉት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋናዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ሰልጣኞች በቆይታቸው ያገኟቸውን ክህሎቶች በተግባር ላይበማዋል የስራ ውጤታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በስልጠናው ወቅት ስለጀነሬቲቭ ኤ.አይ፣ ፕሮምፕት ኢንጂነሪንግ ፣ለመንግስት ስራዎች የሚያገለግሉ የኤ.አይ መተግበሪያዎች እና ስለቴክኖሎጂው መሰረታዊያን
ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል። ይህ ስልጠና ቀደም ሲልበድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለሚገኙ የመንግሥት ሰራተኞች በተመ
ሳሳይ መልኩ የተሰጠ ሲሆን፤በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute