በቻይና ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዪን ሄጁን የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ፡፡
· Visiting
በቻይና ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዪን ሄጁን የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ ስለኢንስቲትዩቱ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስራዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡
ከጉብኝቱ በተጨማሪ ሁለቱ ሀገራት በኤ.አይ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ የኢንስቲትቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ውይይቱ በቻይና እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን በሁኔታዎች የማይቀያየር ስትራቴጂካዊ አጋርነት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ሁለቱ ሀገራት በአቅም ግንባታ፣ በልምድ ልውውጥ እና በኤ.አይ ዘርፍ ኮምፒውቲሽናል ሪሶርስን በትብብር ለማልማት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ዪን ሄጁን በበኩላቸው ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስቀጠል ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በኤ.አይ ዘርፍ ለመስራትና ልምዷን ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን በመግለፅ ውይይቱ የቻይና-አፍሪካ ፎረምን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute