የማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Ministry of Mines Delegation Explores EAII’s AI Solutions for National Development
የማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
በማዕድን ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ብርሃኔ ያዴሳ የተመራው ልዑኩ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘዉዴ ለጎብኚዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ ቁልፍ ዘርፎች ላይ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተሰሩ ችግር ፈቺ ስራዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ቀርቦላቸዋል፡፡
ጎብኚዎቹ የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከል፣ ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት፣ የሮቦቲክስ ስራዎችን እንዲሁም የኤ.አይ ምርት ማሳያ ክፍልን በጉብኝታቸው ወቅት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute