የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ውድድር ይፋ ሆነ፡፡
· Competition
The East African Community and the German government have launched the second AI4EAC technology competition, targeting 20,000 participants across all eight EAC member states and offering $50,000 in prizes to support AI-driven regional innovation.
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (EAC) እና የጀርመን መንግሥት በሁሉም ስምንት አባል አገራት የሚገኙ 20,000 ሰዎችን ያካተተ ሁለተኛውን “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ” (የAI4EAC) የኤ.አይ ውድድር ይፋአድርገዋል። ይህመርሃ ግብር ከቀድሞው አሰራር በአምስት እጥፍ አድጓል፤
ለአሸናፊዎችም 50,000 ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቶለታል።
ይህ መርሃ ግብር በምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (EAC) እና በጀርመን መንግሥት ትብብር የተጀመረ ክልላዊ የቴክኖሎጂ ውድድር እና የስልጠና መርሃ ግብር ነው። ዋናው አላማውም በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የክልሉን ችግሮች የሚፈቱ ፈጠራዎችን ማፍራት እናወጣቶችን ማብቃት ነው።
የመጀመሪያው ዙርውድድር 3,891 ተሳታፊዎችን ያሳተፈ ሲሆን አሁን የተያዘው የ20,000 ግብ በቀጠናው ሀገራት የዲጂታል ክህሎት ክፍተትን ለመሙላት፣ የስራ እድል ለመፍጠር እና የዩኒቨርሲቲ ትምህርትን ለማዘመን ትልቅ እገዛ እንዳለው ተገልጿል።
አይ.ኤ አፍሪካ እንደዘገበው የጀርመን ኢኮኖሚ ሚኒስቴር እና የልማት ኤጀንሲ (GIZ) ከኢስትኢኮ (EASTECO) እና ከኢዩሲአይ (IUCEA) ጋር በመተባበር መርሃ ግብሩን እየመሩት ይገኛሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute