“የጋራ ትርክት ለጋራ ሀገር” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ ሰነድ ላይ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ።
· Other
EAII Staff Discuss “Common Narrative for a Common Country” to Support National Unity and Peace
በሀገርዓቀፍ ደረጃ ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው “የጋራ ትርክት ለጋራ ሀገር” በሚል መሪ ቃል በሰላም ሚኒስቴር በተዘጋጀ ሰነድ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል።
የሐገረመንግሥት ግንባታ፣ ሀገራዊ ማንነት፣ ብሔራዊ ጥቅሞች፣ የሀገራዊ እሴቶቻቾን ምንነት እና አሰባሳቢ የሆኑ ትርክቶች እንዲሁም የጋራ ትርክት ገንብተው ስኬታማ የሆኑ ሀገራት ተሞክሮ በሰነዱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ሀሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ተጨማሪ ግብአቶች በውይይቱ ተሳታፊዎች ተነስቷል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለማምጣት የሚረዱ እና የሀገርን የሰላም ግንባታ ሂደት ያግዛሉ ያሏቸውን ሀሳቦች አንስተዋል፡፡
በዉይይቱ ማጠቃለያ ላይ የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ኃላፊዉ አቶ ከበደ ቶሎሳ ባደረጉት ንግግር በሰነዱ ላይ በተደረገው ውይይት ሀገራዊ አውድን የተከተሉ እና ጠቃሚ ግብአቶች ተገኝተዉበታል ብለዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute