"የዘመኑ የውጊያ አውድ የሆነውን የቴክኖሎጂ የበላይነትና የተወዳዳሪነት አቅምን ማሳደግ ይገባል" አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር
· Other
Day of Resilience honors security institutions and calls for stronger national unity.
የኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል"የጽናት ቀን" የፌዴሬሽን ምክር ቤትአፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስተት የስራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታናየደህንነት ተቋማት አመራርንና አባላት፣ ጀግኖች አርበኞች እንዲሁም ጥሪየተደረገላቸው ተሳታፊዎች በተገኙበት በአድዋ ሙዚዩም በድምቀት ተከብሯል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ባለፉት የለውጥ አመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በመቋቋም ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ
ወደ ሆነ ለውጥ እንድትሸጋገር በማድረግ የጎላ አበርክቶ አኑረዋል ብለዋል። አፈ ጉባኤው በንግግራቸውየጽናት ቀንክብረ በዓል ሲከበር ሀገርን ከፍ በማድረግ የፀና የሉአላዊነትጋሻና የፅናት ተምሳሌት የሆኑትን የፀጥታና የደህንነት ተቋማትን ማሰብና መዘከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
የዘመኑ ውጊያ አውድ የሆነውን የሳይበር ደህንነትና የቴክኖሎጂንየበላይነት አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አሳስበዋል፡፡ በክብረ በዓሉ የማይናወጥብሔራዊ አንድነት ለመገንባት የተለየ ትኩረት በመስጠት በአንድነት መቆም እንደሚገባ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት የሰሯቸውን ስራዎች የሚዘክሩ ሁነቶች በመድረኩ ቀርበዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute