የጀሚኒ ኤ.አይ አገልግሎቶች በአፍሪካ ሀገራት ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በነጻ ሊቀርቡ መሆኑን ጉግል አስታወቀ።
· AI Investment
Google Empowers African Students with Free Access to Gemini AI Tools, Advancing Tech-Driven Education and Innovation Across Six Countries.
ኩባንያው አፍሪካዊያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሰረታዊ የሆኑ የኤ.አይ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ በማሰብ ነዉ ለ6 ዩኒቨርሲቲዎች ይህንን ዕድል ያመቻቸዉ። አገልግሎቱንም በደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ዚምባቡዌ፣ ሩዋንዳ፣ ናይጄሪያ እና ጋና የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማግኘት ይችላሉ።
ተማሪዎቹ የጉግል አገልግሎት የሆኑትን የጀሚኒ 2.5፣ ዲፕ ሪሰርች፣ ቪኦ 3፣ 2 ቴራ ባይት የክላዉድ ስቶሬጅ እንዲሁም የጉግል ፕሮ ፕላን የዓመት ነጻ አቅርቦት የሚያገኙ ይሆናል።
ድጋፉ ተማሪዎች በትምህርታቸዉ ዉጤታማ እንዲሆኑና የምርምር እና የፈጠራ ስራዎቻቸዉን ለማገዝ የተደረገ መሆኑን የኩባንያው ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute