በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የሚታገዙ የሬዲዮ ኔትዎርኮች ለአፍሪካ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ቀጣዩ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ እየሆኑ ነው።
· AI Solutions
As data demand surges and digital services expand, African telecom operators are turning to AI-RAN to optimize spectrum use, reduce costs, and deliver higher-quality, more resilient network services.
የአፍሪካ የቴሌኮም ኩባንያዎች የዳታ ፍጆታ መጨመርና የላቀ የዲጂታል አገልግሎት ፍላጎትን ለማሟላት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚታገዙ የሬዲዮ ግንኙነት ኔትዎርኮችን ተግባራዊ እያደረጉ ነው።
ይህ ዘዴ ማሽን ለርኒንግን ከኔትዎርክ አስተዳደር ጋር በማዋሃድ የሃብት አጠቃቀምን ለማሻሻል፣ የአገልግሎት ጥራትን ለመጨመር እና ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ ለመተንበይ ያስችላል። ይህም የኔትዎርክ መጨናነቅን በመቅረፍ እና የዳታ ፍጥነትን በመጨመር እንዲሁም የኃይል ፍጆታን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ አለው።
እንደ ኤሪክሰን ያሉ ዓለማቀፍ ኩባንያዎች እና ቴክኖሎጂውን በተግባር ያዋሉ ኩባንያዎች ሕብረት አባላት ለዚህ ቴክኖሎጂ እድገት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ እያደረጉ ነው።
ቴክኖሎጂው የአፍሪካ የቴሌኮም አውታረ መረቦች ይበልጥ ፈጣን፣ አስተማማኝ እና የደንበኞችን ፍላጎት ያማከሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በዚህም የአህጉሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያፋጥን ቁልፍ መሳሪያ ተደርጎ ይወሰዳል ሲል ኤ.አይ አፍሪካ ድረገፅ አስነብቧል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute