የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የበጀት ዓመቱን የ9 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቀረበ።
· Other
EAII Presents Nine-Month Report Showcasing AI Innovation, Startup Growth, and National Productivity Achievements
ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በኢንስቲትዩቱ ችግር ፈቺ የኤ.አይ ሥርዓቶችን ከማልማት፣ ተግባራዊ ከማድረግ እንዲሁም ስታርታፖችን ከመደገፍ አኳያ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር አብራርተዋል።
ከምርምር ባሻገር በነበረው የስራ ጊዜ የኢንስቲትዩቱ ባለ 15 ወለል ህንፃ ዋና መስሪያ ቤት፣ ለስታርታፖች ምቹ ሥነ ምህዳር የተፈጠረበት ባለ 5 ወለል ህንፃ እንዲሁም የፈጠራ ማዕከል የሆነው ኤ.አይ ዩኒፖድ ወደ ስራ መግባታቸው በጉልህ ተነስቷል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ ኤ.አይን መሰረት ያደረጉ ሲስተሞች መልማታቸው እንዲሁም በተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች ለሚገኙ የመንግሥት ሰራተኞች ስለ ኤ.አይ መሰረታዊያን ስልጠና መሰጠቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ኢንስቲትዩቱ ሀገራዊ በሆኑ ሁነቶች እና ተልዕኮዎች ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ዋና ዳይሬክተሩ ባቀረቡት ሪፖርት ጠቁመዋል።
የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት እፀገነት መንግስቱ በበኩላቸው በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በመረጃ አሰባሰብ ጥናትና ምርምር ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን፤ ኢንስቲትዩቱ አቋሙን በስራ ያስመሰከረ ከመሆኑም ባሻገር ባለፉት 9 ወራት ያስመዘገበው አፈጻጸም ውጤታማና ለሌሎች አርዓያነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute