ጉግል በ15 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ዳታ ሴንተር በህንድ ሊገነባ ነው፡፡
· AI Investment
Google Launches $15 Billion AI Infrastructure Hub in Southern India, Joining Global Tech Giants in Fueling the Nation’s AI and Data Center Boom.
ጉግል አልፋቤት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በህንድ የኤ.አይ መሠረተ ልማት ማዕከል ለመገንባት 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ ይህም በፍጥነት በማደግ ላይ ባለችው ህንድ የሚያደርገው ቅልቁ ኢንቨስትመንት ይሆናል፡፡
የአሜሪካ ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መዋዕለ ንዋያቸዉን በህንድ በማፍሰስ ላይ ሲሆኑ ጉግልም አንዱ ሆኗል፡፡ አማዞን በደቡብ እስያዊቷ ህንድ በ2030 የክላውድ መሠረተ ልማት ለመገንባት 12.7 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ማቀዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ኦፕን ኤይ.አይም በቀጠናው ባለ1 ጊጋዋት የመረጃ ቋት ለመገንባት ይፈልጋል።
በአጠቃላይ በአካባቢው በዳታ ሴንተር መሠረት ልማት ግንባታ ውስጥ ያሉ ኢንቨስትመንቶች በ2027 ወደ100 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድጉ ይጠበቃል።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር እና ሚሊዮኖችን ከድህነት ለማውጣት ቴክኖሎጂ ቁልፍ ነው ማለታቸውን የብሉምበርግ ዘገባ ያመለክታል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute