አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ማሳያ መድረክ የሆነዉ ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል 2025 (GITEX GLOBAL ) መካሄዱን ቀጥሏል።
· Study Shows
GITEX GLOBAL 2025 Showcases Cutting-Edge AI Innovations, Including UAE’s Smart K-2 Patrol Car, as Global Tech Leaders Unite to Shape the Future of AI Governance.
በዱባይ በመካሄድ ላይ የሚገኘዉ 45ተኛዉ ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል 2025 የኤ.አይ ቴክኖሎጂን የተላበሱ አዳዲስ ፈጠራዎች ተዋዉቀዉበታል። በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ዝናን ያተረፉ እንደ ኦራክል፣ አማዞን እና አይ.ቢ.ኤም ያሉ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎቶቻቸዉን ለዕይታ አቅርበዋል።
በሁነቱ ከተዋወቁት የቴክኖሎጂ ዉጤቶች አንዱ ኬ-2 በተባለ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያ የተዋወቀዉ በኤ.አይ የታገዘ የፖሊሶች የቁጥጥር መኪና ነዉ። መኪኖቹ በሚገጠምላቸዉ ስርዓት አማካኝነት ከቪዛ እንዲሁም ከነዋሪነት ጋር የሚያያዙ ወንጀሎችን የፈጸሙ አካላትን መለየት ያስችላሉ።
ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል የዘርፉ አንቀሳቃሾች ያካበቱትን ልምድ የሚጋሩበት፣ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የሥነ ምግባር ትግበራና ቁጥጥርን የተመለከቱ ዉይይቶች የሚደረጉበት ነዉ። እንዲሁም ተሳታፊዎች ዓለማቀፍ የገበያ ትስስር የሚያገኙበት ሁነት ሆኖ ለዓመታት በመካሄዱን እንደቀጠለ ነዉ። ኢትዮጵያም በዚህ ደማቅ የቴክኖሎጂ ሁነት በመሳተፍ ላይ ትገኛለች።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute