የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አብሮ ለመስራት ተስማሙ
· MOU
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute and the FDRE National Defense Force signed a Memorandum of Understanding to strengthen defense capabilities through artificial intelligence in areas including cybersecurity, logistics, training, healthcare, air operations, and electronic warfare.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተደራጀ ዘመናዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እና ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ በስምምነቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን እድገት ማስመዝገብ የቻለ ሀገራዊ ተቋም ነው ሲሉ አድንቀዋል።ዘርፉ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል በማልማት ረገድ መደመር የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ መቋቋሙ ለኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የሀገር ሉዓላዊነትን እና ብሄራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ ዘመናዊ ሰራዊት ለማደራጀት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመከላከያ ኃይል በተለይም በአየር፣
በምድር እና በሳይበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።ኢንስቲትዩቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በሎጀስቲክስ፣ በስልጠና፣ በሳይበር ደህንነት፣ በመከላከያ ሰራዊት ጤና አጠባበቅ፣ እንዲሁም በአየር ኃይል እና በኤሌክትሮኒክስ ዋርፌርዘርፎች በኤ.አይ በመታገዝ የሠራዊቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ አበይት ጉዳዮችን ያካተተ ነው።
በክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እና ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ ከስምምነቱ በተጨማሪ የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute