ኦፕንኤአይ “ዶትስ” የተባለ አዲስ ረዳት ይፋ አደረገ
· Other
OpenAI Introduces “Dots,” Customizable Autonomous Assistants Designed to Handle Complex Digital Tasks with Minimal Supervision
ሳን ፍራንሲስኮ ውስጥ በተካሄደው ዓመታዊ የልማት ቀን መድረክ ላይ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን፤ ዶትስ በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ፣ ውስብስብስራዎችን በብቃት መወጣት የሚችሉ እና እንደ ዲጂታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሊያገለግሉ የሚችሉ አስደናቂ ረዳቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
እነዚህ ረዳቶች ተጠቃሚዎች በስራ በተጠመዱ ጊዜ እንደ ዲጂታል ረዳት እንዲያገለግሉ በቀለማት ያሸበረቁ እና በደንበኛው ምርጫ ሊስተካከሉ በሚችሉ የካርቱንመልክ በቀረቡ አቫታሮች ተወክለዋል።
ዶትስ እንደ ሶፍትዌር ማልማት፣ ዌብሳይት መገንባት፣ የዳታ ትንተና ማከናወን እና የዕለት ተዕለት መርሃ ግብሮችን መያዝ የመሳሰሉ የተለያዩ ሥራዎችን በራሳቸውየክላውድ ኮምፒዩተር አማካኝነት ማከናወን ይችላሉ።
እንደ ቢቢሲ መረጃ ለዶትስ ኃላፊነት ከተሰጣቸው፤ በትክክል ይከውናሉ፡፡ ውሳኔ ሲፈልጉ ብቻ ተጠቃሚውን በድጋሜ ያነጋግራሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute