የናጎያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
· Visiting
Nagoya University Researchers Visit the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to Explore Knowledge Transfer and Future Collaboration
ከጃፓን ቀደምት እና ታዋቂ የምርምር ማዕከላት አንዱ የሆነው የናጎያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ቡድን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ፤ ኢንስቲትዩት በሕግ ማስከበር፣ በጤና፣ በግብርና፣ በፍትሕ እንዲሁም ሀገርኛ ቋንቋዎችን የማሽን መገልገያ ቋንቋ ለማድረግ በቴክኖሎጂው ታግዞ እያከናወናቸው ስለሚገኙ ተግባራት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የጉብኝቱ ዓላማ የእውቀት ሽግግር ላይ ያተኮረ ሲሆን በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ሊሠሩባቸው በሚችሉባቸው የትብብር መስኮች ላይም ውይይት ተካሂዷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute