“አገር የምትገነባዉ በተቋም ግንባታ ነዉ፤የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ደግሞ የዚህ ማሳያ ነዉ።”’ አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት.
· Other
University of Gondar Commends EAII’s Indigenous AI Innovation and Expands Collaboration for Digital Transformation
ኢንስቲትዩቱ አገርን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየሰራ ያለውን ዘመን ተሻጋሪ ስራ ያደነቁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) “አገር የምትገነባው በተቋም ግንባታ ነው፤ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም የዚህ ትክክለኛ ማሳያ ነው” ብለዋል። በተለይም ኢንስቲትዩቱ ያበለጸጋቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሲስተሞች ችግር ፈቺ እና ሀገር በቀል መሆናቸው ለየት እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ተቋሙ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። የዩኒቨርሲቲውአመራሮች ኢንስቲትዩቱ በቴክኖሎጂ የበለጸገችዋን የነገዋን ኢትዮጵያ በግልጽ የሚያሳይና ቀጣይነት ያለው ለውጥ የሚያሳይ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል። በጉብኝት መርሃ ግብሩ የኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን የሚያሳይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute