የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሀዋሳ ከተማ በሁለት ትምህርት ቤቶች የኤ.አይ ክበባትን አቋቋመ፡፡
· Education
EAII Launches AI Clubs at Hayole Fura and Alamura Schools to Empower Student Innovation
ኢንስቲትዩቱ በሀዮሌ ፉራ ሞዴል አካዳሚ እና በአላሙራ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የኤ.አይ ክበባትን አቋቁሟል፡፡
በክበባቱ ምስረታ ወቅት የየትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስለሰሯቸው ስራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ ተማሪዎቹ የክበቡ ምስረታ በትክክለኛ ሰዓት የመጣ መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በሀዮሌ ፉራ ሞዴል አካዳሚ ፕሮጀክት ማኔጀር አቶ ሽመልስ አየለ በክበቡ ምስረታ ወቅት የክበቡ መመስረት ተማሪዎች በዘርፉ ክህሎታቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ የአላሙራ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ቃሊሞ አቅሙ እያላቸው ተገቢውን ድጋፍ ማግኘት ላልቻሉ ተማሪዎች የክበቡ ምስረታ እንደ ትልቅ እድል የሚወስዱት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በምስረታ መረኃ ግብሮቹ ላይ ኢንስቲትዩቱ ለታዳጊዎች የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እነደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute