የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዘመቻን በቅሊንጦ ኢንደስትሪ ዞን አከናወነ::
· Other
The management and staff of the Ethiopian Artificial Intelligence Institute planted more than 14,000 predominantly indigenous and edible seedlings at Kilinto Industrial Park as part of Ethiopia’s nationwide campaign to plant 800 million seedlings in a single day.
የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል፤ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ ተሳታፊ ሆነዋል። በዚህም የአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በቅሊንጦ ኢንደስትሪ ዞን ዛሬ ረፋዱን ተካሂዷል።
በመርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የዋና ዳይሬክተሩ የቴክኖሎጂ አማካሪና የፅህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ባለፉት ዓመታት የተተከሉት ችግኞች የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር ከመጠበቅ ባሻገር፣ ለምግብነት የሚውሉና ሀገር በቀል በመሆናቸው ከፍተኛ አገራዊ ፋይዳ አላቸው ብለዋል።
በዕለቱ የተሳተፉት አመራር እና ሰራተኞች በበኩላቸው ለሀገርና ለወደፊት ትውልድ ዘላቂ ጥቅም ባለው በዚህ ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በዘመቻው ከተተከሉት ከ14 ሺህ በላይ ችግኞች መካከል አብዛኞቹ ለምግብነት የሚውሉና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ናቸው። ከዚህ ቀደም የኢንስቲትዩቱ አመራር እና ሰራተኞች ሐምሌ 23፣ 2018 ዓ፣ም በቢሾፍቱ ከተማ በተመሳሳይ የችግኝ ተከላ ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute