የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጎንደር ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኤ.አይ ክበባት አቋቋመ፡፡
· Education
EAII and the University of Gondar launch AI clubs in three schools to empower students with future-ready skills.
ኢንስቲትዩቱ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በጎንደር ከተማ በሚገኙ ሦስት ትምህርት ቤቶች ላይ የኢንስቲትዩቱ እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በተገኙበት የኤ.አይ ክበባትን መስርቷል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት እና ፋሲለደስ ትምህርት ቤቶች የክበብ ምስረታ የተደረገባቸው ናቸው።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ምስረታውን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት በወጣቶች እና ታዳጊዎች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ብሎም የመጪውን ዘመን ብሩህ ተስፋ በታዳጊዎች ላይ ለማስረፅ በመላ ሀገሪቱ ባሉ ትምህርት ቤቶች የኤ.አይ ክበባት እየተመሰረቱ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) በበኩላቸው ዛሬ ላይ ዓለምን እየመራ ያለውን የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ታዳጊዎች በሚገባ እንዲገነዘቡ በማድረጉ በኩል የኤ.አይ ክበባቱ ቁልፍ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።
በጎንደር ትምህርት ቤቶች የተከተፈቱት የኤ.አይ ክበባት በአካባቢው ያሉ ታዳጊዎች ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ያላቸውን ክህሎት እንዲያሳድጉ እና ለፈጠራ እንዲነሳሱ መሠረት ይሆናቸዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute