ኦፕንኤአይ ሞዴሎች ውሳኔ እንዲሰጡ የሚያስችል አዲስ ኤፒአይ አስተዋወቀ
· AI Solutions
OpenAI Launches Decisions API to Simplify Data Evaluation, Scoring, Probability Assessment, and AI-Agent Deployment
የአሜሪካው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኩባንያ ኦፕንኤአይ የኤአይ ሞዴሎች መረጃን ተንትነው ከተሰጡ አማራጮች እንዲመርጡ፣ የይሆናልነት መጠን እንዲገልጹ እና በተወሰነ መለኪያ ነጥብ እንዲሰጡ የሚያስችል "ዲሲሽንስ ኤፒአይ" (Decisions API) ይፋ ማድረጉን ኤአይ ዴይሊ ፖስት ዘግቧል።
አዲሱ አገልግሎት ከነባሩ የመልስ ኤፒአይ ጎን ለጎን የሚሠራ ሲሆን ከጽሑፍ ማመንጨት ይልቅ በተለየ ተግባር ላይ ውሳኔ በመስጠት ላይ ያተኩራል። የቴክኖሎጂ አበልጻጊዎች ጽሑፍና ምስል በማስገባት ሞዴሉ በተቀመጠው መስፈርት እንዲገመግምና ውጤቱን በተደራጀ መልኩ እንዲመልስ ማድረግ ይችላሉ።
ከዚህ ቀደም ገንቢዎች ኤአይን በሥራ ሂደት ለመጠቀም የራሳቸውን የመለያ ደንቦች፣ የትክክለኛነት መለኪያዎችና የማረጋገጫ ሥርዓቶች ለየብቻ ማበልጸግ
ነበረባቸው። አዲሱ ኤፒአይ ይህን ሂደት በማቅለል የኤአይ ኤጀንቶችን ወደ ተግባር የማስገባት ጊዜን ሊያሳጥር ይችላል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute