ኤአይ ለባህላዊ የእጅ ጥበብ
· Other
BRICS+ Fashion Summit Highlights AI’s Role in Transforming Traditional Craftsmanship for Global Markets
በቅርቡ በሞስኮ በተካሄደው የብሪክስ+ የፋሽን ሴሚናር ላይ ከ60 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተገናኝተው ነበር። ውይይታቸው ያጠነጠነው አንድ ጥያቄ ላይ ነው፤ የፋሽን ቴክኖሎጂ እና ባህላዊ የእጅ ሥራ እንዴት ተባብረው ይወዳደራሉ? ቴክኖሎጂ ከባህላዊ ዕውቀት ጋር ሲጣመር ፈጠራ ያድጋል፤ ቅርስም ለዘመኑ ገበያ ይደርሳል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዲዛይነሮችን እየረዳ ነው። ሥራቸውን ያፋጥናል፣ አዳዲስ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ እንዲሁም የምርት ወጪያቸውንም እንዲቀንሱ እየረዳቸው ነው።
ለኢትዮጵያ ይህ ትልቅ ዕድል ነው። ሀገራችን የሽመና፣ ጥልፍ፣ ቆዳ ውጤቶችና የልዩ ልዩ እጅ ሥራ አልባሳት ባለቤት ናት። እነዚህ የዘመናት ቅርሶች ከኤአይ ጋር ሲዋሃዱ አዳዲስ የዲዛይን ሐሳቦች ይፈልቃሉ፤ ይህም ለዘርፉ ትልቅ ዝላይ ይሆናል። የምርት ጥራት ይሻሻላል፣ ጊዜና ወጪ ይቀንሳል፣ ለዓለም ገበያ የሚመጥኑ ማራኪ ምርቶችም ይቀርባሉ።
ከዚህም ባሻገር የባህላዊ የእጅ ሥራ ዕውቀትን በዲጂታል መንገድ መመዝገብ ያስችላል። ይህ ዕውቀት ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ያደርጋል፤ ለወጣቶችና ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። የኢትዮጵያን ባህላዊ ሀብትም ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይለውጣል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute