የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ::
· Education
EAII Empowers Young Women Through AI Training to Build Digital Skills, Innovation Capacity, and Future Competitiveness
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላቋቋመው የኤ.አይ (AI) ክበብ አባላት የሰጠው ይህ ስልጠና ተማሪዎቹ ከዘመናዊው ቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን መስተጋብር እንዲያሳድጉ እና ስለ ዘርፉ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመሠረታዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጽንሰ-ሀሳቦች እንዲሁም በማሽን ለርኒንግ እና ፕሮግራሚንግ ምንነት እና ተግባራዊነት ላይ ትኩረቱን አድርጓል።
ስልጠናውን የወሰዱ ተማሪዎች በበኩላቸው፣ የቴክኖሎጂውን አቅም በአግባቡ ለመረዳት መቻላቸውን ገልጸው፣ የተገኙትን መሰረታዊ እውቀቶች ለወደፊት የፈጠራ ስራዎቻቸው እንደ መነሻ እንደሚጠቀሙባቸው እና ለዘርፉ ያላቸውን ተነሳሽነት በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀሰቀሰላቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተማሪዎችን በዘርፉ ብቁ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለውን ግብ ለማሳካት፣ በመላ ሀገሪቱ በተቋቋሙ የኤ.አይ ክበቦች እየሰጠ ያለው ስልጠና ተጠናክሮ ይቀጥላል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute