የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
· MOU
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እና የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ በአቅም ግንባታ፣ በስልጠና እና በቴክኒካል ድጋፎች ዙሪያ በትብብር በመስራት የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ዘርፉን ለማዘመን እና ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ስምምነቱን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ከምስረታው ጀምሮ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሰው ኃይልን ለማብቃት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል። አክለውም ይህ ስምምነት ዘርፉን በመጀመሪያ ዲግሪ በመስጠት ደረጃ ቀዳሚ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል። ይህን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በሚኖረዉ ስራም ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።
የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው ስምምነቱ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ላይ በጋራ በመስራት የትምህርት ስልጠና መስኮችን የበለጠ ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። ስምምነቱ ለኤ.አይ እና ለሮቦቲክስ ኢንተለጀንት ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የሰው ኃይል ፍላጎትን ለማሟላት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute